First General Assembly – May 2012

Amb Zewde Retta – Key Note Speech

TMSAANA First GA, May 27 2012

ተፈሪ መኰንን ለ ኢት ዮ ጵ ያ

ዋሽንግተን ዲሲ
ግንቦት 19 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም

27/5/12
ከ ዘ ውዴ ረ ታ

ተፈሪ መኰንን! ለኢትዮጵያ የተከበራችሁ ወዳጆችና ጓደኞች፤

ለአእምሮአችሁ ብርሃን ከፍቶ ያሳደጋችሁንና ወደ ቁም ነገር ያሸጋገራችሁን፤ የተፈሪ መኰንንን ትምህርት ቤት የ ቀድሞ ተማሪዎች ማህበር በሰሜን አሜሪካ ስትመሠርቱ፤ የመጀመሪያው አስተያየት አቅራቢ እንድሆን የሰጣችሁኝን ክብር የተቀበልኩት እጅግ በጋለ ደ ስ ታ ነ ው፡ ፡ ለ ብ ዙ ዎ ቻ ች ሁ አ ብ ሮ አ ደ ግ ጓ ደ ኛ ች ሁ ና ለ እ ኔ ም የ ቤ ተ ሰ ብ ወ ን ድ ሜ የ ሆ ነ ው ል ጅ ጴጥሮስ አክሊሉ፣ ለዚህ ለቀድሞ ተማሪዎች ማህበር አመሠራረትና በተለይም ስመጥር የ ሆነ ው የተፈሪ መኰንን መታሰቢያ ከተከበረው ቦታው እንዲመለስ፤ ምን ያህል እንደሚደክምና ምን ያህል አጥብቆ እንደሚጥር በቅርብ ያየሁት ስለሆነ፤ ያለኝን አድናቆትና ምሥጋና የማቀርብለት ከልብ ከመነጨየጋለ ስሜት ጋር ነው፡፡

ጴጥሮስ አክሊሉ ከልጅነቱ ጀምሮ አስተዳደጉንና የቁም ነገር ጉዞውን የማወቅ ዕድል ያጋጠመኝ ስለሆንኩ፤ ባመነበት ፀንቶ የሚገኝ፤ በሚያስበው ጠንክሮ የሚቀጥል፤ የሚጣልበትን እምነትና የሚሰጠውን አደራ ተቀብሎ የመፈጸምና የማስፈጸም ሰፊ ችሎታ ያለው ስለሆነ፤ ምር ጫች ሁ ት ክ ክ ለ ኛ ውን ና ጠን ካ ራ ውን መስ መር የ ጨበ ጠ ነ ው፡ ፡ እ ኔ ም ዛ ሬ በ መካ ከ ላ ች ሁ ተገኝቼ ለመናገር የበቃሁት፤ በወንድማችን በጴጥሮስ አክሊሉ ጥረትና አዘጋጅነት ነው፡፡

የተከበራችሁ ወዳጆቼ፤

ዛሬ እንግዳችሁ ሆኜ ለመናገር ከፊታችሁ የቀረብኩት የሰባ ሰባት ዓመት ወጣት፤ ራስ ተፈሪ መኰንን ኋላ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ በትምህርት አሳድገው ለኢትዮጵያ አገልግሎት እንዲደርሱ ካበቋቸውአራት ትውልዶች ውስጥ፤ በሦስተኛ ደረጃ ከሚመደቡት መካከል ነኝ፡፡

ሁላችሁም እንደምታውቁት፤ ተፈሪ መኰንን የዛሬ ዘጠና አምስት ዓመት፤ የኢትዮጵያ መን ግ ሥት ባ ለ ሙሉ ሥልጣን አ ልጋ ወራሽ ከ ሆኑ በ ት ቀ ን ጀምሮ፤ ለ አ ምሳ ስ ምን ት ዓ መታት አገራችንን በመሩበት ዘመን ውስጥ፤ እያከታተሉ የአራት ትውልድ ፍሬዎችን አስተምረው ለአገር አስተዳደር ኃላፊነት ያበቁ ታላቅ መሪ ናቸው፡፡ ይህም የሚያሳየን፤ የተፈሪ መኰንን የትምህርት ወላጅነት ከአባትነት እስከ ቅም አያትነት ደረጃ የደረሰ መሆኑን ነ ው፡ ፡

ከጥንት ጀምሮ ያለውን፤ የሠለጠነውዓለምየተጓዘበትን የመሪዎች ታሪክ ስንመለከት፤ አንድ መሪ የአገሩን ተወላጅ ከመጀመሪያ ትምህርት ቤት አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ

አስተምሮ፤ ለመንግሥት ኃላፊነ ት አ ብ ሮ ለ መሥራ ት የ ቻ ለ ፤ ከ ተ ፈ ሪ ታውቃላችሁ፡ ፡ የ ተፈሪ መኰንንን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለን ስንመረምር፤ እንደ አቆጣጠር በ1916 ዓ.ም የአውሮፓን አገሮች እየተዘዋወሩ በጐበኙበት ጊዜ፤ አገራችንን ከጨለማው ዓለም ወደ ብርሃን ለማሻገር ፍቱን የሆነው መድኃኒት፤ የኢትዮጵያን ልጆች በዘመናዊ ስልት በማስተማር ብቻ መሆኑንና ከዚህም የተሻለ ሌላ አማራጭ አለመኖሩን በጥልቀት እንደተገነዘቡ እንረዳለን፡፡ ጉብኝታቸውን ባካሄዱበት፤ በሥልጣኔ እጅግ በገፉት የአውሮፓ አገሮች ውስጥ፤ የየአገሩ መሪዎች እየተቀበሏቸው ሲያነጋግሯቸው፤ የራስ ተፈሪ

መኰንን የመጀመሪያው የእርዳታ ጥያቄ፤ ተማሪ ቤቶች ሥሩልኝ! የኢትዮጵያን ልጆች አስተምሩልኝ!የሚል ነበር፡፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት፤ በዚያን ጊዜ በሥልጣኔ የገፉትና

በኰሎኒዎች ሐብት እየበለጸጉ ሕይወታቸውን ያመቻቹት የአውሮፓ መንግሥታት መሪዎች፤ ተፈሪ መኰንን የሚያልሙትን የትምህርት እርዳታ ለመለገሥ ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ በዚያን ዘመን የኮሎኒያሊስቶች መሠረታዊ አቋምና ዕምነት፤ የአፍሪካ ሕዝቦች ለጌቶቻቸው የጉልበት አገልግሎታቸውን እንዳያቋርጡ፤ ባይሆን ከበሽታ የሚድኑበትን የመከላከያ መድኃኒት እንዲያገ ኙ ያደርጋሉ እንጂ፤ በትምህርት አእምሮአቸው እያደገ አስተሳሰባቸው እየ ዳበረ የነገ የነፃነት ጠያቂዎች እንዲሆኑባቸው ጨርሶ አይፈልጉም ነበር፡፡ በዚያን ዘመን ምንም እንኳ አገራችን ነፃነቴን አላስነካም ብላ፤ በብዙ ተጋድሎ በዓለም ቤተሰብ ውስጥ ግዛቷን

ከሚኒስትርነ ት እስከ መኰን ን በ ስ ተ ቀ ር ጠቅላይ ሚኒስትርነ ት ደረጃ ሌ ላ መጥ ቀ ስ እ ን ደ ማይ ቻ ል ያደረሰና ሁላ ችሁም ኢትዮጵያ አስከብራ ሕይወቷን የቀጠለች ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ ከሠለጠነችና ከተሻሻለች፤ አፍሪካውያኖች አደገኛ ምሳሌ ትሆናለች ተብላ የምትፈራ ስለሆነ፤ ኮሎኒያሊስቶቹ ከበው መውጫና መግቢያ በማሳጣት፤ ብዙ ግፍ ሲፈጽሙባት መቆየታቸው መቸውንም አይደለም፡ ፡

ለሌሎቹ ዙሪያዋን የሚዘነጋ ስለዚህም፤ ተፈሪ መኰንን በሥልጣኔ የ ገ ፋውን የ አውሮፓን ዓለም ከየመንግሥታቱ በተለይም ከፈረንሣይና ከእንግሊዝ፤ ለኢትዮጵያ የሥልጣኔ በር መክፈቻ የሚሆን እርዳታ ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ሁሉ ሳይሣካላቸው ቀረ፡፡ ሆኖም ተስፋ ሳ ይ ቆ ር ጡ፤ ባ ላ ቸ ው አ ቅ ም ሁ ሉ በ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዘ መ ና ዊ ው ን ት ም ህ ር ት ለ ማ ስ ፋ ፋ ት ቆ ር ጠ ው ተነ ሱ፡ ፡

ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው፤ ተፈሪ መኰንን ዋና ዋናዎቹን የአውሮፓ አገሮች በመጐብኘትና የየመንግሥታቱን መሪዎች በማነጋገር ለአንድ መቶ አርባ ቀናት ከቆዩ በኋላ ሲጐበ ኙ፤ ወደ አገራቸውወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ፤ የዚህ ሁሉ ጉዞ ውጤቱ ምንድን ነው?በሚል መንፈስ፤ መሳፍንትና መኳንንት ብዙ ጥያቄዎች ደርድረው እንደሚጠብቋቸው የታወቀ ነበር፡፡ የዋሒቷ ንግሥት ዘውዲቱ ምኒልክ፤ ከልባቸው የሚያምኑት፤ የራስ ተፈሪን ከዚያ ሁሉ ረዥም ጉዞ በደህና ወደ አገር መመለስን እንጂ፤ ለሌላው ጉዳይ ይህን ያህል ቁም ነገር ሰጥተው የሚያስቡበት አልነበረም፡፡ ነሐሴ 29 ቀን 1916 ዓ.ም፤ ንግሥቲቱ አልጋወራሻቸውን

ከረዥሙጉዞአቸው እንኳን ደህና ተመለስክ! ብለው አንገታቸውን አቅፈው የተቀበሏቸው፤ እጅግ ል ብ በ ሚነ ካ ን ግ ግ ር ነ በ ር ፡ ፡

ልጄ ሆይ!

“ … የዛሬ አምስት ወር ገደማ ወደ ፈረንጆች አገር ለመሄድ ስትሰናበተኝ፤ የተለያየነው በሐዘን እንባ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በማይሳነው አምላክ ፈቃድ፤ በደህና ተመልሰህ ለአገርህ ስትበቃ፤ የምቀበልህ ከደስታ በመነጨእንባ ነው… ”ንግሥቲቱ ይህንን የእናትነትና የጋለ የናፍቆት ስሜታቸውን ለአልጋወራሻቸውሲገልጡ፤

እንባ ሲተናነቃቸው ይታይ ነበር፡፡ ነገር ግን ከንግሥቲቱ ጋር ሆነው ራስ ተፈሪን ለመቀበል በቤተመንግሥቱ የ ተሰበሰቡት መሳፍንትና መኳንንት የ ሚያቀርቡት ጥያቄ፤ የአልጋወራሻችን ወዳጆች የሆኑት ፈረንጆች፤ ለእኛ ምን እርዳታ አቀረቡልን? ወደፊትስ ምን ያስቡልናል?…የሚል ስለሆነ፤ አጥጋቢውን መልስ ለመስጠት ለተፈሪ መኰንን ቀላል አልነ በረም፡ ፡

እንደሚታወሰው፤ በዚህ ከአውሮፓ አገሮች በሚጠየቅ እርዳታ ጉዳይ፤ የአልጋወራሹና የየመሳፍንቱ አስተያየት፤ ቀድሞውንም እጅግ የተለያየ መሆኑ በግልጽ የሚታይና የሚታወቅ ነበር፡፡ መሳፍንትና መኳንንት፤ የተፈሪ መኰንን ወዳጆች የሆኑት ፈረንጆች፤ እውነት የኢትዮጵያ ወዳጆች ከሆኑ፤ ለነፃነታችን መከላከያና ለጠረፍ ግዛቶቻችን መጠበቂያ የጦር መሣሪያዎች ካልሰጡን፤ ሌላው ዋጋ የለውም ብለው የሚያምኑ ነበሩ፡፡ ራስ ተፈሪ ደግሞ፤ ከአውሮፓ አገሮች ከሁሉ አስቀድሞ ኢትዮጵያ የምትጠይቀው እርዳታ፤ ለሥልጣኔ እርምጃ መድኃኒት ነው ተብሎ የታመነበትን ለዘመናዊ ትምህርት ማስፋፊያ የሚሆኑትን፤ የትምህርት መጻሕፍቶችና መምህራኖችን ለማግኘት መጣር፤ ከሁሉ በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ብለ ው ያ ምና ሉ፡ ፡

ለማናቸውም፤ መሳፍንትና መኳንንት እንደተመኙት የጦር መሣሪያዎችን ሆነ ወይም ደግሞ አልጋወራሹ ያሰቡበትን የትምህርት እርዳታ ጉዳይ፤ የአውሮፓ መሪዎች ሳይቀበሉት በመቅረታቸው፤ ተፈሪ መኰንን ባዶ እጃቸውን ተመልሰዋል፡፡

ተፈሪ መኰንን፤ የአውሮፓን ጉብኝት ፈጽመውአዲስ አበባ በተመለሱ ልክ በስምንተኛው ወር፤ የመንግሥትን ሆነ የባለፀጐችን እርዳታ ሳይጠይቁ፤ በግል ገንዘባቸው ብቻ ይህንን ተፈሪ መኰንን ተብሎ በስማቸው የተሰየመውን ትምህርት ቤት ሕንፃ ሠርተው፤ ለኢትዮጵያ ልጆች በፈረንሣዊኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የዘመናዊ ትምህርት መስጫእንዲሆን፤ ሚያዝያ 19 ቀን 1917 ዓ.ም መርቀው ከፈቱ፡ ፡

ይህ አዲስ የተከፈተው የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት፤ የመማሪያ መጻሕፍቶቹንና መሣሪያዎቹን አሟልቶ፤ መምህራኖቹን ደልድሎ፤ ተማሪዎቹን ለመቀበል በሩን ከፍቶ ሲጠባበቅ፤ ባልታሰበ መንገ ድ ዘመናዊውን ትምህርት ለመማር ወደ ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት የ ሚመጡ ወጣቶችን፤ በብዛት ለማግኘት ሳይችል ቀረ፡፡ ይህ ዘመናዊ የተባለው የፈረንጅ ትምህርት፤ የሃይማኖታችንና የባሕላችን ፀር ነው የሚለውን ፕሮፓጋንዳ በመከተል፤ መሳፍንትና መኳንንት፤ ባለፀጋና ቀሳውስት፤ እንዲሁም የኦርቶዶክስ የክርስትና ዕምነት አጥባቂ የሆነው የድሐው ቤተሰብ ጭምር፤ ልጆቻችንን ወደ ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት አንልክም ብለው አ ደ ሙ፡ ፡ በ ጣ ም የ ሚ ያ ስ ገ ር መ ው ፤ ዘ መ ና ዊ ው ን ት ም ህ ር ት በ ዳ ግ ማ ዊ ም ኒ ል ክ ተ ማ ሪ ቤ ት የሚማሩት ወጣቶች ምንም እንኳን ቁጥራቸው ጥቂቶች ቢሆንም፤ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ አልተጠየቁም፤ ወይም አልታዘዙም፡፡ የዚህም ዋናው ምክንያት፤ ተወዳጁ ንጉሣችን ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፤ ፈረንጆች ወደ አገራችን ገብተው ሃይማኖታችንንና ባሕላችንን እንዳያረክሱብን፤ መከላከያውን ዘዴ ስለአዘጋጁልን አደጋው ይደርስብናል ብለን አንሰጋም፡ ፡ አልጋወራሽ ተፈሪ ግን ከፈረንጆች ጋር መቀራረብንና መወዳጀትን በማስፋፋት፤ የ አገ ራችንን አስተዳደር ወደ እነሱ ለመለወጥ ሌት ተቀን የሚሠሩ በመሆናቸው፤ ከዚህም በላይ ሃይማኖታችንንም ከእነሱ ጋር ከማቀራረብ የማይመለሱ መስለው ስለታዩን፤ እሳቸው ባቆሙት ተማሪ ቤት እንዲማሩ ልጆቻችንን አንልክምብለውወሰኑ፡፡

እንግዲህ! ራስ ተፈሪ ምን ማድረግ ይሻላቸዋል? ምንም እንኳ የመሳፍንትና የ መኳ ን ን ት ቤ ተ ሰ ብ ፤ ል ጆ ቻ ቸ ውን ለ ማስ ተ ማር ወ ደ ተ ፈ ሪ መኰን ን ተ ማሪ ቤ ት አ ን ል ክ ም ማለታቸው ባያስገርምም፤ የድሆቹ ቤተሰቦች ግን እስከዚህ ድረስ እርምጃ መውሰዳቸው ከቶ የሚጠበቅ አልነበረም፡፡ ራስ ተፈሪ ከአልጋወራሽነት ማዕረግ በላይ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ ቢሆኑም፤ ሀይማኖትን ተመርኩዞ የመጣባቸውን ተቃውሞ፤ በሥልጣን ተቋቁሞ ለማክሸፍ የሚያስችል ኃይል አልነበራቸውም፡፡ እንደሚታወቀው በሀይማኖት ምክንያት ለሚጫረውጠብ መፍትሔመስጠቱ ቀላል አይደለም፡፡ ለምሳሌ፤ የዛሬ ዘጠና አምስት ዓመት፤ ልጅ ኢያሱን ከሥልጣን ለማውረድ መሳፍንቱና መኳንንቱ፤ መሐል ሰፋሪውንና ሕዝቡን አስተባብረው ለመወሰን የቻሉት በብዙ ምክንያቶች ቢሆንም፤ ከሁሉም ይልቅ በሃይማኖት ጉዳይ እንደነበረ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ተፈሪ መኰንን ለገጠማቸው ችግር መፍትሔ ለማግኘት፤ ለጊዜው የታላላቆቹን ቤተሰቦች ጉዳይ ወደ ጐን ትተው፤ ከድሐው ወገን የተወለዱት ልጆች ተማሪ ቤት ገብተው ለመማር ፈቃደኞች ከሆኑ፤ በየወሩ ደሞዝ ይከፈላቸዋል የሚል የማባበያ ዘዴ ፈጠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙዎቹ ቤተሰቦች፤ ልጆቻቸው የውጭ አገር ትምህርት ተምረው ከሚቀስሙት ዕውቀት ይልቅ፤ በየወሩ የሚከፈላቸው ገንዘብ፤ የኑሮ መደገፊያ ይሆነናል ብለው ስለጓጉ፤ ልጆቻቸውን ወደ ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት ለመላክ መሽቀዳደም ጀመሩ፡፡

እንደምታውቁት፤ በጥንታዊውም ሆነ በዛሬው ዓለም ገንዘብ የማይማርከው የለም፡፡ ተፈሪ መኰንን በፈጠሩት ዘዴ፤ በትጋት እንማራለን የሚሉትን ተማሪዎች በብዛት በማግኘታቸው በ ጣ ም ደ ስ ሲ ላ ቸ ው፤ ም ን ጊ ዜ ም የ ማ ይ ተ ኙ ላ ቸ ው ተ ቃ ዋ ሚዎ ቻ ቸ ው እ ን ደ ገ ና ሌ ላ ች ግ ር አጠመዱባቸው፡ ፡ መሳፍንቱና መኳንንቱ፤ ንግሥተ ነ ገ ሥታት ዘውዲቱ ዘንድ እየ ሄዱ፤ “…የሀይማኖታችንና የባሕላችን ፀር መሆኑ የታወቀውየፈረንጅ ትምህርት መስፋፋቱ፤ ከፍ ያለ ጭንቅ ላይ ሲጥለን፤ አሁን ደግሞ መልካም ምግባር ያላቸውን ልጆቻችንን እያታለሉ ወ ደ ዚ ሁ ተ ማሪ ቤ ት ለ መክ ተ ት ፤ ከ መን ግ ሥቱ ሳ ጥ ን እ ን ደ ሠ ራ ተ ኛ በ የ ወ ሩ ደ ሞዝ እንዲከፈላቸው መደረጉ፤ እጅግ የሚያስገርምና የሚያሳዝን ሆኖብናል … ” በማለት፤ በአልጋወራሹ ላይ ከፍተኛ ቅሬታቸውን አቀረቡ፡ ፡ እንደዚሁም በእነ ዚሁ በታላላቆቹ ሰዎች  አነ ሳሽነ ት፤ የ ቤተክህነ ት ኃላፊዎችም ከመኳንንቶቹ አደረጉ፡ ፡

  • ኧረ ለመሆኑ ይኸ ሁሉ የት ነውየሚያደርሰን?
  • አገራችን የተከበረ ባሕሏና ታሪኳ የሚጠነክርበትን ሳይሆን፤ የሚጠፋበትን መንገድ እንድትከተል አልተደረገም ወይ?
  • አገራችን፤ ልጆቿን በትምህርት ለማነፅ የሚያስችሏት፤ በሊቃውንቶች የተመሰከሩ ብዙ የባሕል ጥበቦች እያሏት፤ የጠላቶቻችንንና የአጥፊዎቻችንን ተንኮል ለመገብየት ለምን ት ደ ክ ማለ ች ?
  • ለአገራችን በውነት የሚታሰበው፤ ዕውቀትን ለማበልጸግና ትምህርትን ለማስፋፋት ከሆነ፤ ለጠላቶቻችን የተንኮል ትምህርት ወጪከመከንዳት፤ አማርኛና ግዕዝን፣ ዜማና ቅኔን፣ ድጓና ጾመድጓን፣ ዝማሬና መዋስዕትን ከመጻሕፍትም ብሉይና ሐዲስ ኪዳንን፤

ልጆቻችን ደህና አድርገው እንዲማሩ፤ ለቤተክህነት መምህሮቻችን ለምን እርዳታ አይደረግላቸውም?እየተባለ ትችቱ በሰፊውቀረበ፡፡

ከዚህ በላይ እንደተገለጸውተፈሪ መኰንን ባላሰቡትና ባልጠበቁት መንገድ፤ ይህ ሁሉ ወቀሳና ተቃውሞ ሲወርድባቸው፤ ምን ያህል እንደአዘኑና ምን ያህል እንደተበሳጩ፤ በዚያን ጊዜ የእርሻ ሚኒስቴር ዋና ዲሬክተር የነበሩት አቶ መኰንን ሀብተወልድ፤ ከብዙ ዓመታት በኋላ ታሪኩን አስታውሰው ለወንድሞቻቸው ሲያስረዱ እኔም እንደአጋጣሚ አጠገባቸው ስለነበርኩ፤ የመስማት ዕድል አጋጥሞኛል፡፡ መኰንን ሀብተወልድ የራስ ተፈሪ የቅርብ ባለሟል በመሆናቸው፤ በዚያን ጊዜ አልጋወራሹ የቅሬታ ስሜታቸውን የገለጹት እንደሚከተለው ነበር ብለዋል፡፡ “…እኔ ይህን ተማሪ ቤት በግል ገንዘቤ ሠርቼ፤ በስሜ“ተፈሪ

መኰንን” ብዬ ሳቋቁም፤ ከንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ጀምሮ እነ ጌታ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስና ሌሎቹም ታላላቆቹ መኳንንቶች፤ በስማቸው አንዳንድ ተማሪ ቤት እየሠሩ፤ ለአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አዲስ ብርሃን ይከፍቱለታል ብዬ ከፍ ያለ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ነገር ግን በቅን መንፈስ ተነሳስቼ ለኢትዮጵያ ሥልጣኔ ትልቅ ውጤት ይሰጣል ብዬ የሠራሁት ሁሉ፤ ሌላ ያልሆነ ትርጉም ከተሰጠው፤ ያለኝ አቅም ጉዳዩን ለንግሥተ ነገሥታት ዘ ውዲ ቱ ምኒ ል ክ በ ግ ል ጽ ና በ ጠነ ከ ረ መን ፈ ስ ማመል ከ ት ካ ል ሆ ነ በ ስ ተ ቀ ር ሌ ላ መን ገ ድ አይታየ ኝም … ” ብለው ወሰኑ፡ ፡

ደግነትና የዋህነት የሚያጠቃቸው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ፤ ሁለት ሐሳቦች ላይ ወደቁ፡፡ በአንድ በኩል ስለውጭአገር ትምህርት አደገኛነት የተነገራቸውሁሉ እውነት መስሎ ሲያታቸው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ልጄ ወንድሜ የሚሏቸው አልጋ ወራሻቸው፤ የአገራችንን ሀይማኖትና ባሕል የሚጐዳ ነገር ይሠራል ብለውለማመን አቃታቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ንግሥቲቱ አንድ አቋም መውሰድ ተቸግረው ከፍ ያለ ጭንቅ ላይ መሆናቸውን ራስ ተፈሪ ሲሰሙ፤ የሚከተለውን ማስታወሻ በብዕራቸውጽፈውአቀረቡላቸው፡፡

ግርማዊት ንግሥት! እናቴ እመቤቴ ሆይ፤

“…ታላቁ ንጉሠ ነገሥታችን አባትዎ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፤ ኢትዮጵያን ወደ ሥልጣኔ ለመምራት መሠረት ነው ብለው ያመኑበትን የፈረንሣዊኛና የእንግሊዝኛ ትምህርት ለማስተማሪያ በስማቸው ባቋቋሙት ተማሪ ቤት፤ በመጀመሪያ እኛን የታላላቆቹን ልጆች ምሳሌ ሆነን እንድንማር ካደረጉ በኋላ፤ ትልቁ ምኞታቸው የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ ዘመናዊውን ዕውቀት እንዲገበዩበት ዕድል ለመስጠት እንደነበረ፤ እናቴ እመቤቴ ከማንም ይበልጥ የሚያውቁት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እኔም ልጅዎ በመጀመሪያ የዳግማዊ ምኒልክ ተማሪ ቤት የመማሪያው ክፍሎች እንዲስፋፉና ብዙ ተማሪዎች ለመቀበል እንዲቻል ያደረግኩት፤ ቀጥሎም ሕንፃውን በግል ገንዘቤ አሠርቼ፤ ተፈሪ መኰንን የተሰኘውን ይኸን አዲስ ተማሪ ቤት የከፈትኩት፤ የአባትዎን የታላቁ ንጉሠ ነገሥታችንን መሪ ሐሳብ ተከትዬ ነው፡፡

በዚህም መሠረት፤

1ኛ/ በዳግማዊ ምኒልክና አዲስ በተከፈተው በተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት፤ ለኢትዮጵያ ልጆች የሚሰጠው ትምህርት፤ የፈረንጆቹን የሥልጣኔ ጥበብ ለመቅሰም የሚያስፈልገውን ብቻ እንጂ፤ ስለውጭአገር ሀይማኖትና ባሕል ማስተማር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን፣

2ኛ/ የአባትዎን የታላቁ ንጉሠ ነገሥታችንን ዓርዓያ በመከተል፤ ቤተሰቦቻቸው እጅግ ች ግ ረ ኞ ች ለ ሆ ኑ ት ተ ማ ሪ ዎ ች ፤ ት ም ህ ር ታ ቸ ውን በ ት ጋ ት ለ መ ከ ታ ተ ል እ ን ዲ ች ሉ ፤ የእርሳስና የወረቀቶች ማለት ደብተሮች መግዣ የሚሆን መጠነኛ የገንዘብ እርዳታ ማድረጋችን፤ በድሐውሕዝብ ዘንድ የሚያስመሰግነን እንጂ፤ የሚያስወቅሰን አለመሆኑን የኢትዮጵያ ንግሥተ ነገሥታት እናቴ እመቤቴ እንዲያውቁልኝ፤ ዝቅ ብዬ በታላቅ ትሕትና እለምናለሁ … ”

ፊርማ
ልጅዎ ታዛዥዎ ራስ ተፈሪ መኰንን

ከዚህ በላይ እንደታየውአልጋወራሽ ተፈሪ በላኩት ማስታወሻ፤ “… የውጭአገር ትምህርት እንዲስፋፋ ያደረግኩት፤ የአባትዎን የታላቁ ንጉሠ ነገሥታችንን መሪ ሐሳብ ተከትዬ ነው…”ሲሉ የገለጹት፤ ንግሥቲቱን እጅግ ያስደሰተና የማረከ፤ ለተጨነቁበትም ጉዳይ የተረጋገጠ ዋስትና የሰጠ ስለሆነ፤ ዘውዲቱ ምኒልክ ከመሳፍንቱና ከመኳንንቱ፤ እንዲሁም ከቤተክህነት መሪዎች የቀረቡላቸውን ስሞታዎች፤ ምንም እንኳ ትክክል አይደለምብለውለመቆጣት ባይደፍሩም፤ በለሰለሰ አነጋገር አለመቀበላቸውን የሚገልጽ መልስ ሰ ጡ፡ ፡

ከንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ወለቱ ለዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የተላከ የተሰጠ መልስ

“ … ስለ ተማሪዎች ደሞዝና ስለ ሐይማኖት ትምህርት ስለአቀረባችሁልኝ ጉዳይ፤ ልጄ ወንድሜአልጋወራሽ ተፈሪን ጠይቄው፤

አንደኛ/ በተማሪ ቤቶቹ ውስጥ ከእኛ ሀይማኖትና ባሕል ውጭ የፈረንጆቹን ጉዳይ ማስተማር ጨርሶ የተከለከለ መሆኑን፤

ሁለተኛ/ ለተማሪዎቹ ደሞዝ ተቆረጠላቸው የተባለው፤ ቤተሰቦቻቸው ችግረኞች ለሆኑባቸው ልጆች፤ የመማሪያ እርሳስና ወረቀቶች ለመግዣ የሚሰጥ እርዳታ እንጂ፤ እንደ መንግሥት ሠራተኛ የወር ደሞዝ የተመደበ አለመሆኑን አረጋግጦ ስለነገረኝ፤ እናንተምይህንኑ እንድታውቁት ይሁን…”በማለት ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ የሰጡት መልስ፤ የተቀዋሚዎቹን ሐሳብ ያከሸፈው ስለሆነ፤ ለራስ ተፈሪ መኰንን ትልቅ ድል ሆነ፡፡

  • –  ከዚህ በኋላ ነው! ተፈሪ መኰንን አብዛኛውን የሥራ ጊዜያቸውን በትምህርት ጉዳይ ላይ በማዋል፤ ለመማር የሚፈልጉ ብዙ ወጣቶችን ለመሰብሰብ የቻሉት፣
  • –  ከዚህ በኋላ ነ ው! ተፈሪ መኰንን ለወደፊቲቱ ኢትዮጵያ ኃላፊነ ትን ለመቀበል የ ሚችሉትን ወጣቶች፤ የ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አስጨርሰው ለከፍተኛው ትምህርት ወደ ውጭአገር ለመላክ የቻሉት፣
  • –  ከዚህ በኋላ ነው! ተፈሪ መኰንን የችግረኞችን ቤተሰብ ልጆች እየረዱ በማስተማር የሕዝብ ወገን መሆናቸውን ስለአሳዩ፤ የመሳፍንትና የመኳንንት አድማ አያሰጋኝም ብለውበልበ ሙሉነት ለመሥራት የቻሉት፡፡ጥቅምት 21 ቀን 1919 ዓ.ም ከዳግማዊ ምኒልክና ከተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤቶች፤ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላሳ ሦስት (33) ወጣቶችን ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጭ አገር ለመላክ በመቻላቸው፤ ተፈሪ መኰንን በሕይወት ዘመናቸው ካጋጠማቸው ትልቅ ደስታ አንዱ እንደሆነ በሰፊው ሲናገሩት ሰምተናል፡፡ በአንድ ጊዜ እነዚህ ሰላሣ ሦስት ተማሪዎች ወደ ውጭ አገር ሲጓዙ፤ አልጋወራሹ ባሰናበቷቸው ዕለት፤ ከተማሪዎቹ ወኪልና

ከራስ ተፈሪ መኰንን የ ተገ ለጹት ስሜቶች፤ ምንጊዜም በታሪክ የ ሚታወሱ መሆን ይገ ባቸዋል፡ ፡

ሞገስ ወልደዮሐንስ የተባለው ወጣት፤ በራሱና በሠላሳ ሁለቱ ጓደኞቹ ስም ሆኖ ባደረገው ንግግር፤ “ … ዓለምን ያዳነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ደቀመዝሙሮቹን የመረጠው ከታናናሾቹ ወገን እንጂ፤ ከታላላቆቹ አልነበረም፡፡ እነሆ አሁንም ልዑል ጌታችን ኢትዮጵያን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር የመረጧቸው አገልጋዮች ከሕዝቡ መካከል ስለሆነ፤ ፍሬያቸውን ለማየት እንዲያበቃዎ አምላካችንን እንለምነዋለን…”በማለት የገለጸውአስተያየት፤ በዘመኑ የአገራችን ሕዝብ የነበረውን አስተሳሰብ የሚያመለክት ሆኖ እናገ ኘዋለን፡ ፡ ራስ ተፈሪም በበኩላቸው፤ ለኢትዮጵያ ሕይወትና ዕድገ ት፣ አንድነ ትና ኃይል፣ ምን ያህል አሸናፊ እንደሆነ፤ መለያየትና መበታተን ደግሞ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ አጥብቀው ካስረዱ በኋላ፤ “ … እኔ ሰው ነኝ ሟች ነኝ፡፡ ለማትሞተው አገራችን ረዳት እንድትሆንዋት እግዚአብሔርን እለምንላችኋለሁ…”ሲሉ የተናገሩት ልብ የሚነካ ቃል፤ የተማሪዎቹን መንፈስ በደስታና በሀዘን አሸብሮት ነበር፡፡ ወጣቱ ሞገስ ወልደዮሐንስ እንደተናገረው፤ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በንጉሠ ነገሥትነት ዘመናቸው፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ ብዙዎቹን ዋና ዋና ሚኒስትሮች የ መረጧቸው፤ ከነ ዚሁ ከመጀመሪያ ደረጃ አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ካስተማሯቸው ከሰላሣ ሦስቱ ተማሪዎች መካከል እንደነበረ ብዙዎቻችን በዕድሜያችን ደርሰን አይተነ ዋል፡ ፡

የተከበሩ ሊቀመንበር

ዛሬ እዚህ ተሰብስባችሁ የምናያችሁ የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች፤ ከእናንተ በፊት የ ነ በሩትና ከእናንተም በኋላ የ ቀጠሉት ለተወደደች አገ ራችን ፍሬያማ አገልግሎት ያበረከታችሁና መልካም ዝና ያተረፋችሁ በመሆናችሁ፤ በታሪክ ላይ አክብሮትና አድናቆት የሚገባችሁ ናችሁ፡፡

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሚያዝያ 1917 ዓ.ም ጀምሮ ለአምሳ ዓመታት “ተፈሪ መኰንን” የ ተባለውን መልካም ስም ይዞ ሲኖር፤ በመስከረም 1967 ዓ.ም ደርግ መጥቶ አለአግባብ ቢሰርዘውም፤ በዚህ ዓለም የተጓደለ ፍርድ ለዘለዓለሙ ፀንቶ ስለማይኖር፤ የተማሪ ቤቱ ትክክለኛው ስምና መሠረታዊው ክብሩ እቦታው ተመልሶ እንደምናየው ምን ጊዜም ተስፋ አንቆርጥም፡፡ “ተፈሪ መኰንን” ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ፤ በአምሳ ዓመታት ውስጥ ያመረታቸውፍሬዎች ሁሉ፤

– ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነትና አንድነት፤

– ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኔ ዕድገት፤

– ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰላም ሕይወት፤

በብዙ ሥራዎች ላይ የተካፈሉና መስዋዕትነትን እስከመቀበል የደረሱ በመሆናቸው፤ የ ቀድሞዎቹ የ ተፈሪ መኰንን ተማሪዎች መቸውንም የ ሚረሱና ሳይታሰቡ የ ሚታለፉ አይደሉም፡፡ የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ካመረታቸውፍሬዎች መካከል፤

–በካቢኔ ሚኒስትርነት ስንቶቹ ከፍተኛ ኃላፊነትን ተቀብለውግዳጃቸውን እንደፈጸሙ፤

-በጦር መኰንንነት ስንቶቹ ለአገር ነፃነት ተዋግተውከፍተኛ ጀብዱ እንደሠሩ፤

-በትምህርት ጉዳይ ስንቶቹ፤ በአስተማሪነትና በከፍተኛ ደረጃ መሪነት፤ ጠቃሚየሆኑ አገልግሎቶች እንዳበረከቱ፤
-በኤኮኖሚና በልማት መስክ ስንቶቹ፤ የአገሪቱን ሕይወት ለማሻሻል ምን ያህል ፕላን እንደገነቡና ምን ያህል ጥረት እንዳደረጉ፤
-በአስተዳደርና በዳኝነት ስንቶቹ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብት ጥበቃና ሰብዓዊ ተግባር ምን ያህል እንደታገሉ፤

እያንዳንዳችን በተለያየ መንገድ የምናውቅላቸው ስለሆነ፤ እነዚህ የቀድሞዎቹ የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ምርቶች ላበረከቷቸው አገልግሎቶች ሁሉ፤ አድናቆታችንና ምሥጋችን ምንጊዜም አይለያቸውም፡፡

የተከበሩ ሊቀመንበር፤

የተከበራችሁ ወዳጆችና ጓደኞች፤

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ አገራችንን ለመምራት ኃላፊነትን ከተቀበሉበት ገና ከአልጋ ወራሽነታቸውዘመን ጀምሮ ለሥልጣኔ መሠረት የሆነውን ትምህርት ለማስፋፋት ቆርጠው ሲነ ሱ፤ በዘመኑ ከነ በረው ኋላ ቀር አስተሳሰብና አመለካከት ጋር፤

– ምን ያህል እንቅፋትና ግጭት እንደአጋጠማቸው፣

– ምን ያህል ትዕግሥትና ጥንካሬ እንደጠየቃቸው፣

ከዚህ ከተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ጋር በማያያዝ ባጭሩ ለማስረዳት ሞክሬአለሁ፡፡

ሁላችሁም እንደምታውቁት፤ ንጉሠ ነገሥት ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያን ልጆች በጠቅላላ፤ በተለይ ደግሞ የድሆቹን ቤተሰቦች ለማስተማር ያደረጉት ብርቱ ጥረት፤ እስከምን ድረስ እንደሆነ ፤ ቀጥሎም በዘመነ መንግሥታቸው ውስጥ ለሀያ ሁለት ዓመታት የ ትምህርት ሚኒስትርነቱን ሥራ በቀጥታ ራሳቸው ይዘው እንዴት ባለ ትጋት ይመሩት እንደነበረ፤ በ መ ጨረ ሻ ም ከ አ ባ ታ ቸ ው ከ ራ ስ መ ኰ ን ን በ ው ር ስ ያ ገ ኙ ት ን መ ላ ው ን የ ግ ል ን ብ ረ ታ ቸ ው ን ሰጥተው፤ የመጀመሪያውን ዩኒቨርሲቲ እንዴት እንዳቋቋሙና የዚሁ ዩኒቨርሲቲም የመጀመሪያው ቻንስለር ሆነውእንዴት ባለ ብርታት ሲሠሩ እንደቆዩ፤ በዕድሜደርሰን ያየነውና የሥራውም ተካፋይ ለመሆን ዕድል ያጋጠመን ሁሉ፤ ምሥክርነ ታችንን በይፋ ከማቅረብ ወደኋላ የ ምንል አይደለንም፡ ፡

ሁላችንም እንደአስተዋልነው፤ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በዘመነ መንግሥታቸው ያለማቋረጥ ለፈጸሟቸውበጐተግባሮችሁሉ፤ የመመስገን ዕድልያላቸውሰውአልነበሩም፡፡

-የተፈሪ መኰንንን ትምህርት ቤት ሕንፃውን በግል ገንዘባቸው ሠርተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በተለይም ለደሐው ቤተሰብ ልጆች አበረከቱ ሲባል፤ የተቀዋሚዎቻቸው ድምፅ የሚያስተጋባው፤ ገንዘቡን ከገባሮቻቸው ሰብስበው ነው እንጂ፤ የግላቸው አይደለም የ ሚል ነ በ ር ፡ ፡

-አዲስ አበባ ላይ ከአባታቸው የወረሱትን ሰፊ ንብረት ዩኒቨርሲቲ አቋቋሙበት ተብሎ ሲነገር፤ ጠላቶቻቸው በሀሰት ፕሮፓጋንዳቸው ሲፈነጩየከረሙት፤ ንብረታቸው በሽያጭ ተተምኖ ገንዘቡን ከመንግሥቱ ሳጥን ወስደው ነው እንጂ በነፃ የተሰጠ አይደለም እያሉ ነበር፡፡

-ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያ ልጆች የመማር ዕድላቸው እንዲሰፋ፤ የትምህርት ሚኒ ስ ት ር ነ ቱ ን ሥል ጣ ን ራ ሳ ቸ ው ይ ዘ ው ይ ሠ ራ ሉ ሲ ባ ል ፤ ጠ ላ ቶ ቻ ቸ ው የ ሚተ ቹ ት ፤ ለፕሮፓጋንዳው ጥቅም እንጂ የእሳቸው ሚኒስትርነት ከሌሎቹ የተሻለ እርምጃ የሚያደርግ ሆኖ አይደለም በማለት ነበር፡፡

እንግዲህ! ለዚህ ሁሉ መሠረተ ቢስ ወሬ ማስረጃው ምንድን ነው? ተብሎ ቢጠየቅ፤ መልሱን “ምንም” ! ከማለት በስተቀር ሌላ መሆን አይችልም፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተቋቋመ ጊዜ፤

የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት ክቡር አቶ ይልማ ዴሬሣና ኋላም እሳቸውን የተኩት ክቡር አቶ ማሞ ታደሰ፤ ንጉሠ ነገሥቱ የገነተ ልዑል ቤተመንግሥታቸውን ለዩኒቨርሲቲው ሲሰጡ፤ ከመንግሥቱ ግምጃ ቤት የተቀበሉት አንድ ሳንቲም አለመኖሩን ደህና አድርገው አረጋግጠዋል፡፡ በደርግ ዘመን ስም አጥፊዎች የሆኑትም የጠላት ወገኖች እየመረጡ የመለመሏቸው ኢንስፔክተሮችና ኦዲተሮች፤ በአራት መንታ ተሰልፈው ሲሯሯጡ ቢከርሙም፤ ከመንግሥቱ ሣጥን የጐደለ የአንድ ሳንቲም ሂሣብ እንኳ ማግኘት አልቻሉም፡፡

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በዚህ ዓለም በኖሩበት በሰማንያ ሦስት ዓመት ዕድሜያቸው ውስጥ፤ ሰባውን ዓመታት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዕድገትና ሥልጣኔ ሲደክሙና ሲቃትቱ የኖሩ በመሆናቸው፤ ከሕዝባቸው አስበልጠው ለራሳቸው ሕይወትና ምቾት የሚያስቡ እንዳልነበሩ፤ ይኸው እውነተኛ ታሪክ እየተገለጠምሥክርነቱን ሰጥቷል፡፡

የተከበሩ ሊቀመንበር!

ወደ ዋናው መነሻዬ ልመለስና፤ ዛሬ የመሠረታችሁት የዚህ የተፈሪ መኰንን የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ዓላማ፤ እያንዳንዳችሁ በልጅነት ዘመን ዕውቀትን የቀሰማችሁበት ትምህርት ቤት፤ እያደገና እየሰፋ ብዙዎቹን ወጣቶች በዘመናዊ ሥልት እንዲያመርትና ታሪኩን ለማስከበር ስለሆነ፤ ሐሳባችሁ እጅግ የሚደገፍ፤ ድካማችሁ ፍሬ የሚሰጥ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ የምታስቡትንና የምታቅዱትን ሁሉ በተሟላ መንፈስ ለመፈጸም የምትችሉትም፤ ልክ የዛሬ ሰማንያ ሰባት (87) ዓመት ተገንብቶ “ተፈሪ መኰንን” ተብሎ የተሰየመው ይህ ትምህርት ቤት፤ ስሙተመልሶ የክብር ቦታውን ሲይዝ ነው፡፡ ለዚህም ግብ የምታደርጉት ብርቱ ጥረት፤ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ዛሬ መተመን ባይቻልም፤ እንደሚፈጸም ሙሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ዋናውቁምነገርትግላችሁንሳትሰለቹመቀጠላችሁነው፡፡

በእኔ አስተያየትና ጥናት “ተፈሪ መኰንን” ብቻ ሳይሆን፤ እንደዚሁ ስሙያለአግባብ በፍርደ ገምድሎች የተለወጠው የአዲስ አበባም ዩኒቨርሲቲ፤ የተመሠረተበትን ስም መልሶ ማግኘት የሚገባው መሆኑን፤ ትክክለኛ ዳኞችና አስተዋዬች በጋለ መንፈስ እንደሚደግፉት እርግጠኛ ነኝ፡፡ ቀደም ብዬ እንዳስረዳሁት፤ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለዚህ ዩኒቨርሲቲ የግል ንብረታቸውን ሰጥተው በማቋቋም ብቻ ሳይሆን፤ የመጀመሪያው ቻንስለር ሆነው ብዙ የለፉና ብዙ የሠሩ በመሆናቸው፤ በደርግ የተሰረዘው ስማቸው እንዲመለስ በዛሬው ሰዓት የሕዝብ አስተያየት ቢጠየቅ፤ ከመቶ ዘጠናውድጋፉን እንደሚሰጥ በትክክል የሚታመን ነው፡፡ የተፈሪ መኰንን የቀድሞዎቹ ተማሪዎችም፤ ብዙዎቹ ወደ ከፍተኛ ትምህርት የተሻገሩት በዚህ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በኩል ስለሆነ፤ ሐሳቤን እንደምትቀበሉኝ እምነቴ የፀና ነው፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.